፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የካሊፎርኒያ ገዥ በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለማርገብ የፌዴራል መንግስት ድጋፍ አያስፈልገኝም ነበር አሉ፡፡
ሰነድ አልባ ስደተኞች በቀሰቀሱት ተቃውሞ ምክንያት ሪፐብሊካኑ ትራምፕ ብሄራዊ ዘብ ሀይሉን በግዛቷ አሰማርተዋል፡፡
የካሊፎርኒያው ገዥ ጋቪን ኒውሶም ትራምፕ ጦር ማሰማራታቸውን ያጣጣሉት ሲሆን ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ሪፐብሊካኖቹ ያደረጉት ነውም ብለዋል፡፡
የትራምፕ ድርጊት ታስቦበት ውጥረቱን ለማባባስ የተደረገ ነው በሚል ዴሞክራቱ ገዥ ወንጅለዋል፡፡
ዋይት ሀውስ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስደተኞች ተቃውሞ በማስነሳት በአሜሪካ የስደት እና ጉምሩክ (ICE) ሀይሎች ላይም ጥቃት ሰንዝረዋል ብሏል፡፡
የካሊፎርኒያ ግዛት ጉዳይ ዴሞክራቶቹ እና ሪፐብሊካኖቹ የሚጋጩባትን አዲስ መድረክ የከፈተ ሆኗል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካሊፎርኒያ ባለስልጣናት ግዴታቸውን መወጣት ባለመቻላቸው የፌደራል መንግስት ሰላምን ለማስፈን ጣልቃ ለመግባት ወስኗል ብለዋል፡፡
ገዥው ኒውሶም ተቃዋሚዎች በሰላም ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ያሳወቁ ሲሆን የፌደራል ሀይሎች መግባት አግባብነት የሌለው ነው በሚልም ሪፐብሊካኖቹን ወንጅለዋል፡፡
ዲሞክራቷ ከንቲባ ኬረን ባስ ተቃውሞውን እራሳችን መቆጣጠር የምንችለው ነበር ቢሉም ከ1957 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለግዛቷ ፈቃድ ብሄራዊ ዘቡ ወደ ካሊፎርኒያ በትራምፕ ትዕዛዝ ገብቷል፡፡
ሲ ኤን ኤን እና ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግበውታል፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












