45 ሚሊዮኑ ወዲያውኑ የሚከፈል ቀሪው ደግሞ ብቃቱ እየታየ የሚታከል ነው ተብሏል።
ይሁንና የለንደኑ ክለብ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 20 ጎሎችን ላስቆጠረው የ25 ዓመቱ አጥቂ የቀረበለት ገንዘብ በቂ ነው ብሎ የመቀበል ፍላጎት እንደሌለው ዘገባው አስረድቷል።
በሁለቱ ክለቦች መካከል እየተደረገ ያለው ድርድር እንደቀጠለና ብሬንትፎርድ ከዝውውሩ 60 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚፈልግ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ካሜሮናዊው ኢንተርናሽናል የኦልትራፎርዱን ክለብ የመቀላቀል ላቅ ያለ ፍላጎት እንዳለው እየተነገረ ነው።
እምቡሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሊጉ በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 20 ጎሎችን ከማስቆጠሩ በተጫማሪ ለጓደኞቹ ሰባት ጊዜ አመቻችቷል በጎል ብዛት ሀላንድ፣ ኢሳክና ሳላህ ብቻ ይበልጡታል።
እምቡሞ በጂ ቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ያለው ዉል ሊጠናቀቅ 12 ወራት ብቻ ቀርተዋል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












