ልክ በዛሬዋ ዕለት ግንቦት 28 1936 ዓ.ም የመድረክ ፈርጥ የሆነው ወጋየሁ ንጋቱ የተወለደበት ቀን ነው፡፡
ወጋየሁ በአዲስአበባ ቀበና አካባቢ የተወለደ ሲሆን ትምህርቱንም በዳግማዊ ሚኒሊክ እና በተፈሪ መኮነን ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቪርስቲ ተቋቁም በነበረው “ኪነጥበብ ወትያትር” ማዕከሉ ውስጥ ከጓደኞቹ አባት መኩሪያ እና ደበበ እሸቱ ጋር እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀምሮል፡፡ በዛም ዝግጅት እና የፅሁፍ- ተውኔትን መሰረታዊ እውቅትን መማር ቻለ፡፡
ወጋየሁ ንጋቱ የቲያትር ፀሃፊ አዘጋጅ ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛ ነበር ለዚህም በውጭ ሀገራት ሳይቀር የተለያዩ ትምህርቶችን ወስዷል በሞያው ላይ የነበሩ ጓደኞቹ ሲግልፁትም ወጋየሁ ትያትርን የኖራት፤ ያከበራት ድንቅ ልጇ ነበር ሲሉ ይገልፁታል፡፡
ወጋየሁ ንጋቱ እናት አለም ጠኑ፤ አንድ ጡት፤ አሉላ አባነጋ፤ ፍርዱ ለእናንተ እና ሌሎች ብዙ ቲያትሮችን ሠርቷል፡፡ እንዲሁም በሬዲዩና ቴሌቪዥን በሚተላለፉ አጫጭር ተውኔቶችን በማዘጋጀት እና መፀሀፍቶችን በመተረክ አይረሳም ከአድማጮች አዕምሮ የማይጠፉት ፍቅር እስከ መቃብር፤ ማዕበል የአብዮት ዋዜማ፤ ማዕበል የአብዮት መባቻ እና ማዕበል የአብዮቱ ማግስት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ወጋየሁ ንጋቱ ህዳር 6 1982 በ46 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












