በዛሬዋ ዕለት ግንቦት 26 1767 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱት እንስቶች መካከል አንዷ የሆኑት እቴጌ ምንትዋብ ከ250 ዓመት በፊት ያረፉበት ቀን ነበር።
እቴጌ ምንትዋብ የአፄ በካፋ ባለቤት እና የአፄ ኢያሱ ዳግማዊ (የቋረኛ ኢያሱ) እናት ናቸው፡፡ እቴጌ ምንትዋብ 1700 ዓ.ም አካባቢ ቋራ ውስጥ ከአባታቸው ከደጃዝማች መንበር ከእናታቸው ከወ/ሮ እንኮዬ ተወለዱ፡፡
ባለቤታቸው አፄ በካፋ ከሞቱ በኋላ በተከታታይ በነገሡት በልጃቸው ዳግማዊ አፄ ኢያሱ እንዲሁም በአፄ ኢዮአስ ዘመነ መንግሥታት ትልቅ ሚና ነበራቸው።
ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪም ዛሬ ድረስ በበርካታ ጎብኚዎች የሚጎበኙ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንፀዋል። ከነዚህም መካከል የጎንደር ቁስቋም ማርያም፣ የጎንደር መጥምቁ ዩሀንስ እና በጣና ሃይቅ ላይ የሚገኘውን ናግራ ስላሴ ተጠቃሽ ናቸው።
እቴጌ ምንትዋብ በቁንጅናቸው፣ በባልትና ሙያቸውና በፖለቲካ ብቃታቸው ተደናቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ነበሩ።
በ- ሔርሜላ ተመስገን












