። ። ። ። ። ። ። ። ።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በኢስታንቡል በተካሄደው ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ የሰላም ድርድር ተጨማሪ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ በመስማማት ተጠናቋል።
የዩክሬን እና የሩሲያ ልዑካን ድርድር ሶስት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሳይስማሙ ድርድሩ ተቋጭቷል ።
በዚህ ሁለቱም ወገኖች ተጨማሪ እስረኞችን ለመለዋወጥ ብቻ ነው ከስምምነት የደረሱት።
የዩክሬን ተደራዳሪዎች ሩሲያ በድጋሚ ያለ ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ውድቅ ማድረጓን ተናግረዋል።
በቱርክ ኢስታንቡል በተካሄደውና ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀው ውይይት ከሁለቱ ወገኖች የታመሙት እና በከባድ የቆሰሉ የጦር እስረኞችን እንዲሁም ከ25 ዓመት በታች የሆኑትን እስረኞች ለመለዋወጥ ተስማምተዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሁለቱ ወገኖች እያንዳንዳቸው 1,000 የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ከስምምነት መደረሱን ተናግረዋል ።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በበኩላቸው፣ መንግሥታቸው ቮልዲሚር ዘለንስኪን እና ቭላድሚር ፑቲንን ለማቀራረብ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። “የእኔ ፍላጎት ፑቲንን እና ዘሌንስኪን በኢስታንቡል ወይም በአንካራ አንድ ላይ ማምጣት ነው” ሲሉም ተናግረዋል ።
ዘገበው የዘጋርዲያን ነው
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












