Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

“ከሰላም ውጭ ሌሎች አማራጮች አያዋጡም” እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)

"ከሰላም ውጭ ሌሎች አማራጮች አያዋጡም" እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)

May 22, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

May 22, 2025

በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየታቸውን የሠጡት የአማራ ክልል ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት እሸቱ የሱፍ(ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል የጸጥታ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም ከሕዝብ ጋር የሚደረጉ ውይይቶችም እንደጨመሩ ገልጸዋል። “ውይይቶችም ፍሬ እያፈሩ ነው። በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሰላም አማራጮችን የሚመርጡትም እየበዙ ነው። ይህ ደግሞ በክልሉ ያለውን ሰላም የበለጠ ዘላቂ እና አስተማማኝ እንዲኾን እያደረገው ይሄዳል” ያሉት ሀላፊው፣ ስለ ሰላም የሚዘምሩት፣ ስለ ሰላም የሚሰብኩት፣ ስለ ሰላም የሚወያዩት እና ሰላምን ለማጽናት የሚተጉትም በርክተዋል ብለዋል።

“ከሰላም ውጭ ሌሎች አማራጮች አያዋጡም” እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)

በማብራሪያቸውም የአማራ ክልል ባለፉት ጊዜያት በከፍተኛ የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደነበር አስታውሰው፣ ችግሩ ክፉ ጠባሳ የጣለ ክስተት ነበር። በሰው ሕይዎት፣ በንብረት እና በሥነ ልቦና ላይም ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት። አሁን ላይ ግን በክልሉ የተረጋጋ ሰላም አለ፤ በየአካባቢው ያሉ የአሥተዳደር እርከኖች መንግሥታዊ አመራር የሚሰጥባቸው ናቸው ብለዋል። የጸጥታ መዋቅሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማድረግ አቅሙ እያደገ፣ የመፈጸም አቅሙ ከፍ እያለ መሄዱንም አንስተዋል።

ሕዝብን ባለቤት በማድረግ የሰላም ሁኔታውን የበለጠ የተሻለ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውንም ገልጸዋል። ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎች እስከ ቀበሌ ድረስ ወርደው ከሕዝብ ጋር እየተወያዩ ነው ያሉት ኀላፊ፣ አውዳሚ ሃሳቦች እንዲታረሙ፣ ለሰላም እና ለውይይት ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል። የጸጥታ ኃይሉ አካባቢዎችን በተገቢው መንገድ እየመራ እና ሰላምን እያረጋገጠ መኾኑንም አስታውቀዋል። ለአማራ ክልል ሕዝብ የሚበጀው ችግሮችን በውይይት መፍታት ነው ያሉት ኀላፊው ግጭት አውዳሚ ነው፣ የኋላቀርነት አስተሳሰብ መገለጫ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በግጭት ውስጥ የነበሩ ታጣቂዎችም፣ ስህተት መኾኑን እያመኑ፣ የአማራ ክልልን ሕዝብ አጎሳቁያለሁ፤ በድያለሁ እያሉ የሰላም አማራጮችን እየተቀበሉ ነው። ይህን ያመጣው ደግሞ ውይይት ነው፤ ውይይቶቹ ብዙ ነገር ቀይረዋል፤ ውጤትም አምጥተዋል ብለዋል። የአማራን ሕዝብ እና መንግሥት በጠላትነት ከሚያይ ኃይል ጋር አናብርም እያሉ ብዙዎች እየመጡ ነው፤ ሌሎችም ይሄን አካሄድ መከተል አለባቸው ነው ያሉት። ልጆች እንዳይማሩ መፍረድ ምን ማለት ነው? ሲሉ የሚጠይቁት ኀላፊው፣ ግጭት ትውልድን ከመግደል የዘለለ ጥቅም የለውም። የሰላም አማራጮችን እስካሁን ያልተቀበሉትም ቆም ብለው አስበው ሰላምን መምረጥ አለባቸው፤ ምክራችን ይህ ነው ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው።

መንግሥት አሁንም የሰላም አማራጩ ክፍት ነው። በየአካባቢው ካሉ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ጋር እየተነጋገሩ ሰላምን መምረጥ ይገባቸዋል። የእኛ ጀግና እያሉ ሀገር እንዲወድም የሚገፋፉ አይጠቅሟቸውም፣ የሚጠቅማቸው ሰላም እና ሰላም ብቻ ነው ። ኅብረተሰቡም ልጆቹን መምክር፣ ወደ ሰላም መመለስ አለበት። ሁለት ዓመታት ትምህርት ማቋረጥ በቀላል የሚታይ አይደለም። ይሄን ኀይልን ማውገዝ ግድ ይላል፣ አባቶቻችን ሕዝብን እና ሀገርን ከጠላት ነው የተከላከሉት፤ ስለዚህ ሁሉም ለሰላም አስተዋጽኦ እንዲያደርግም ነው የጠየቁት።

፨

ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ 👇

https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
ShareTweetShare
Previous Post

“ባለፉት ዓመታት ችላ ተብለው የቆዩ ቅርሶችን በመጠበቅና በመጠገን ረገድ ከፍተኛ ውጤት ተገኝቷል” የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ

Next Post

የሻዕቢያና የህወሓት ፀሐይ እየጠለቀች ነው – ከ ሌ/ ጀነራል ዮሐንስ ገ/ መስቀል ጋር

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የሻዕቢያና የህወሓት ፀሐይ እየጠለቀች ነው – ከ ሌ/ ጀነራል ዮሐንስ ገ/ መስቀል ጋር

የሻዕቢያና የህወሓት ፀሐይ እየጠለቀች ነው - ከ ሌ/ ጀነራል ዮሐንስ ገ/ መስቀል ጋር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራልን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራልን ጎበኙ

በእስራኤል ላይ የተሰነዘረው ጥቃት

በእስራኤል ላይ የተሰነዘረው ጥቃት

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?