:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ባለፈው ሳምንት በጓንግዶንግ ግዛት በተከሰተ አስገራሚ ክስተት የ24 ዓመቷ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ድንገት የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ችሎታዋን ሙሉ በሙሉ አጣች። ተማሪዋ፣ በቻይና ውስጥ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በምትገኝበት ወቅት በአጋጣሚ ክፍል ውስጥ ከወደቀች በኋላ ነው ይህ ያልተጠበቀ ክስተት የገጠማት።
ከዚህ አደጋ በፊት ማንዳሪን፣ ካንቶኒዝ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ ትናገር የነበረችው ወጣት፣ በተለይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የነበራት ችሎታ ሙሉ በሙሉ እንደጠፋባት የተነገረ ሲሆን ከዚህ ቀደም ያለ ምንም ችግር ትግባባበት የነበረው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለእርሷ እንደ ባዕድ ሆኖባታል።
ክስተቱ ካጋጠማት በኋላ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰደችው ተማሪ፣ የሕክምና ምርመራ የተደረገላት ሲሆን የምርመራው ውጤት እንደሚያመለክተው የአንጎሏ ግራ ክፍል መጎዳቱ የቋንቋ የመናገር ችሎታዋን እንድታጣ ምክንያት ሆኗል።
ችግሩን ለማስተካከል ተማሪዋ የአንጎል ቀዶ ጥገና ተደርጎላታል እንደ መልካም ዜና የቀዶ ጥገናው ህክምና የተሳካ በመሆኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ችሎታዋን መልሳ ማግኘት ችላለች። ይህ ክስተት የሰው አንጎል ምን ያህል ውስብስብ እና ለጉዳት የተጋለጠ እንደሆነ ዳግም አሳይቷል።
ዘገባው የoddity central ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን












