በቡልጋሪያ የመጀመሪያ ዲቪዚዮን የሚወዳደረው አርዳ ካርድዛሊ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ ተጫዋቹ “ፔትኮ ጋንቼቭ ሞቷል” የሚል የተሳሳተ መረጃ ከሌቭስኪ ሶፍያ ባደረጉት ጨዋታ የ3 ደቂቃ የህሊና ጽሎት አድርገውለታል።
የ78 አመቱ የቀድሞ ተጫዋች ጋንቼቭ ካለበት ስፍራ ሆኖ “በሕይወት አለሁ’’ ሲል ድምጹን አሰምቷል።
የቀድሞውን ኮከብ ህልፈት ያሳዘናቸው ቡልጋሪያውያን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርቦ እስኪታይ ድረስ ማመን አልቻሉም ነበር።

“ጨዋታውን ከባለቤቴ ጋር እየተመለከትን ነበር” ያለው ጋንቼቭ “ነፍስህን በገነት ያኑር የሚል ጽሁፍ ያለበት የራሴን ምስል ስንመለከት እና የህሊና ጸሎት ሲደረግልኝ ሳይ በጣም ደነገጥኩ” ሲል ተናግሯል።
“ያለማቋረጥ ለባለቤቴ አጽናኝ መልዕክቶች ሲላኩላት ነበር” የሚለው የቀድሞ ተጫዋች፣ በቀድሞ ክለቡ ድርጊት ማዘኑን ገልጿል።
አርዳ ካርድዛሊ እግር ኳስ ክለብ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ባወጣው መግለጫ ለተፈጠረው ትልቅ ስህተት ይቅርታን ጠይቋል።
“ለጋቼቭ ረጅም እድሜን ከጤንነት ጋር እንመኛለን” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












