ቀያይ ሰይጣኖቹ እያሳለፉ በሚገኙት እጅግ ደካማ የውድድር አመት መነሻነት፣ውድድር አመቱ በዋንጫ ማጠናቀቅ የሚችሉበት ዕድል ካላቸው በአደባባይ ማክበር እንደማይፈልጉ ታውቋል።
ክለቡ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቀጥተኛ ተጽዕኖ መኖሩን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ይገኛል።

የይሮፓ ሊጉን ዋንጫ ከሃገራቸው ተቀናቃኝ ቶተንሃም ሆትስፐር መቀማት ከቻሉ ድሉን በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ብቻ ለማክበር ማሰባቸው ተነግሯል።
ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በዌስትሃም ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ “በዚሁ አቋማችን የምንቀጥል ከሆነ ክለቡን ልለቅ እችላለሁ” በማለት በምሬት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
በማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር መካከል የሚደረገው የይሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአውሮፓውያን ግንቦት 21 በስፔን የሚደረግ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












