በክረምት የዝውውር መስኮት ቡድናቸውን እንደ አዲስ ለመገንባት ያሰቡት ወሃ ሰማያዊዎቹ በኤሲ ሚላኑ አማካኝ ላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
ሲቲ በክረምት ከኬቭን ደብሯይነ ጋር እንደሚለያይ ይፋ የተደረገ ሲሆን እንደ ማቲዮ ኮቫቺች እና በርናርዶ ሲልቫ ያሉ አማካኞችም ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ለኤሲ ሚላኑ አማካኝ አድናቆት እንዳላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ተጫዋቹን በቀጣይ አመት የቡድን ስብስባቸው አባል እንዲሆን ይፈልጋሉ ተብሏል።
ኤሲ ሚላን ለ26 አመቱ አማካኝ 57 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ እንደሚፈልግ ከጣሊያን የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












