NBC Ethiopia
May 12, 2025
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ከጣቢያችን ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ የጊዜ ግስ መድረክ ላይ በነበራቸው ቆይታ እንዳብራሩት በአፄ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የነበረው የዲፕሎማሲ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለው አሁን ባለንበት የብልጽግና ስርዓት መሆኑን ገልፀው ኢትዮጵያ የነበራትን የተሠሚነት አቅም በተሻለ ሁኔታ ወደ ነበረው መመለስ ተችሏል ብለዋል። እየተሠራ ያለው የዲፕሎማሲ ስራ የሀገርን ጥቅም፣ ክብር፣ ሉአላዊነት እንዲሁም የዜጎችን ሠላም ያስጠበቀ መሆኑን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የህዳሴ ግድብ፣ የባህር በር ጥያቄዎች እንዲሁም ከውጭም ይሁን ከውስጥ የነበሩ ግጭቶችን በሠላማዊ መንገድ መፍታት የተቻለው መንግስት በትኩረት በሚሰራቸው የዲፕሎማሲ ስራዎች ነው ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ከጊዜ ግስ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












