፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የእናቱን ስልክ ለመጫወት ብሎ የተቀበለው ህፃን የበይነ መረብ መገበያያ በሆነው አማዞን መተግበሪያ ላይ 70‚000 ከረሜላዎችን ያዛል፡፡
እናት በድንገት የቤቱን በር ስትከፍት በድንጋጤ ትዋጣለች ደጇ በከረሜላዎች ተጥለቅልቆ ታየዋለች በመደናገጥ ልጇን ስትጠይቀው ከረሜላዎቹን እሱ ከመተግበሪያው ላይ እንዳዘዘው ይነግራታል፡፡
በአጠቃላይም በእናቱ ስልክ የ4200 ዶላር ከረሜላዎችን ነበር ያዘዘው እናቱም እንደ መፍትሄ ሃሳብ ብላ ያቀረበችው የታዘዘበትን የበይነ መረብ መገበያያ መተግበሪያ ማናገር ነበር ባደረገችው ጥረትም የተወሰኑ ከረሜላዎችን ድርጅቱ መልሶ እንደወሰደው ያስታወቀች ሲሆን የተቀሩትን ደግሞ ለጎረቤቶቿ እና ለጓደኞቿ ሸጣቸዋለች፡፡
በ- ሔርሜላ ተመስገን












