።።።።።።።።።።።።።።።።።
3ኛው አለምአቀፍ የልማትና የአብሮነት ጉባኤ በመጪው ግንቦት 5 እና 6 በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአፍሪካ ህብረትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ጉባኤውን እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል።
በአፍሪካ ለመጀመሪያው ጊዜ የሚካሄደውን ከቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ አስቀድሞ የሚካሄደው ኮንፍረንሱ አህጉራዊ የሰላም ግንባታ፣ የሰብአዊ ክብርና ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም የልማት ጉዳዮች አጀንዳ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ ለመሳተፍ ከተለያዩ የአለም ሀገራት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ተፅእኖ ፈጣሪዎች እና ሌሎችም ከ80 በላይ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል።
በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው የቡድን 20 አባል ሀገራት የአፍሪካን አጀንዳዎች ለማስተጋባት ኮንፍረንሱ ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሏል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












