::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የቶተንሃም ሆትስፐሩ አሰልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉ፣ አርሰን ቨንገር “የይሮፓ ሊግ አሸናፊ ቡድን የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ሊሆን አይገባም” በማለት ስላቀረቡት ሃሳብ አስተታየታቸውን ሰጥተዋል።
“እንግዳ ነገር ነው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አሰልጣኙ “የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታ ክርክር ያስነሳው የቶተንሀም ለዩሮፓ ሊግ ዋንጫ መቃረብ ነው” ሲሉ ሃሳቡን ተችተዋል።
“ሃሳቡ ለአመታት የቆየ ነው ? ወይስ ባለፉት ቀናት የመጣ ?” ሲሉ የጠየቁት ፖስትኮግሉ፣ የፈረንሳዊውን የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ ሸንቁተዋል።
አክለውም “የቶተንሀም ስም የትም ቦታ ቢቀመጥ ሁሉም ሰው ለማሳነስ እና ለማዋረድ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል” ሲሉ አምርረው ተናግረዋል።
በፊፋ የአለማቀፍ የእግርኳስ ልማት ዘርፍ ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት አርሰን ቬንገር አዳዲስ ህጎች በተለያዩ ውድድሮች ላይ እንዲካተቱ ሃሳብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በ- አልፈሪድ ነስሮ