፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ምዕራቡን ዓለም ብቻዋን ቆማ እየታገለች ነው አሉ።
ምዕራቡ ዓለም ሩሲያን ወደ በርካታ ትናንሽ አገራት የመከፋፈል የረዥም ጊዜ ፍላጎት እንዳለው አስገንዝበዋል ፑቲን።
ፕሬዚዳንቱ ይህን አስተያየት የሰጡት “ሩሲያ፡፡ክሬሚሊን።ፑቲን፡፡25 ዓመታት” የሚል ስም በተሰጠው ዘጋቢ ፊልም ላይ ነው።
በሩሲያ -1 ቴሌቭዥን ተዘጋጅቶ እሁድ የተለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ምዕራቡ ሩሲያ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ጭምር ያስመለከተም ነው ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ፕሬዚዳንትነት ለመጀመሪያ ጊዜ የመጡበትን 25ኛ ዓመት አስመልክቶ የተዘጋጀው ፊልም በርካታ ጉዳዮችን ዳሷል፡፡
ፑቲን በፈረንጆቹ ግንቦት 7-2000 ዓ.ም ነበር ቃለ መሃላቸውን የፈጸሙት፡፡
ለሩሲያውያን የድል ወራቸው ከሆነው ግንቦት ጋር የፑቲን 25ኛ ዓመት በዓለ ሲመት መከበሩ ልዪ ትርጉም እንደሚሰጣቸው ተነግሯል፡፡
ናዚ ጀርመንን ካሸነፉበት የድል ቀናቸው በ2 ቀናት ዝቅ ብሎ የፑቲን 25ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ሲከበር ክሬሚሊን ታሪካዊ መገጣጠሙን ያጎላዋል።
“ሩሲያ ብቻዋን የተሰባሰበውን ምዕራቡን ዓለም እየተጋፈጠች ነው”ያሉት ፑቲን ከ2000 ቀደም ባለው ጊዜም” ውስጥ ውስጡን ሲሰሩብን ነበር” ብለዋል፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ











