በአከባበሩ ላይም ፕሬዚዳንት ታዬ በዐርበኞች መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮችና አባላት፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአከባበሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡