May 3, 2025
የኢትዮጵያ እና አርሜኒያን ታሪካዊ ወዳጅነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአርሜንያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርግሲያንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይቱ ያተኮረው በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ ነው።የኢትዮጵያ እና አርሜንያ ግንኙነት ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት ያለው መሆኑን ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል።ይህን ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በባህል ዘርፎች የበለጠ መጠናከር እንደሚገባው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












