፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የየመን ሁቲዎች እስራኤል ላይ የባሊስቲክ ሚሳዔል ጥቃት ማድረሳቸውን አሳወቁ፡፡
ጥቃት የተሰነዘረው በሰሜናዊ እስራኤል መሆኑን ይፋ ያደረጉት ሁቲዎች እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት እስካላቆመች እርምጃችን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በሃይፋ ከተማ አቅራቢያ ጠዋት ላይ ጥቃቱ ደርሷል ፡፡ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ዒላማ ያደረጉት ሁቲዎች በቀይ ባህር አካባቢ የሚደርስባቸውን የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኃይሎች አጻፋ እንደሚቀለብሱ በተደጋጋሚ ይዝታሉ፡፡
የሁቲው ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬህ ባሊሰቲክ ሚሳዔል ወደ ራማት ዴቪድ የአየር ኃይል ማዘዣ አቅጣጫ ሚሳዔሉ መወንጨፉን እወቁልን ብለዋል፡፡
የእስራኤል ጦር በሃይፋ አካባቢ የአደጋ መቷል ድምጽ ሰጭ ደውሎች የተጠንቀቁ መልዕክት አሰምተዋል የሚል መረጃም አጋርቷል፡፡
ከየመን የተነሳው ሚሳዔል መክሸፉንም አሳውቋል የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይ ዲ ኤፍ) በመግለጫው፡፡
ዘገባው የታይምስ ኦፍ እስራኤል እና የአልጀዚራ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












