የላብ አደሮች ቀን በአለምአቀፍ ደረጃ ግንቦት 1 ወይንም ሚያዚያ 23 ይከበራል።
ሜይ ደይ ወይንም ሌበር ደይ የሚሉ ስያሜዎችም አሉት።
ጅማሮው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1886 በአሜሪካን የሰራተኞች ማህበራት ንቅናቄ ጋር ተያይዞ መሆኑ ይነሳል።
በ 19ኛው ክፍለዘመን በአሜሪካ የኢንደስትሪ መስፉፉትን ተከትሎ በርካታ የስራ እድል ተፈጥሮ ነበር ሆኖም ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት በእነዚህ ተቋማት እስከ 16 ሰአታት መስራትን ይገደዱ ነበር በዚህም ለሞት፣ ለከፍተኛ የጤና ጉዳትና፣ ዘላቂ የጤና ቀውስ ውስጥ ይገቡ ነበር።
ዝቅተኛ ክፍያ፣ በቀን 16 ሰአታት መስራትና ሌሎችንም የሰራተኞች የመብት ጥያቄዎች ባነገቡ ማህበራትና ንቅናቄዎች የስራ ሰአታት በቀን ወደ 8ሰአት ዝቅ እንዲል ሆኗል።
ለዚህ ቀን እውናዊነት በርካቶች የአካልና የህይወት መስዋትነትን ከፍለውበታል።
በአለምአቀፍ የላብአደሮች ቀን ግንቦት አንድ እንዲከበር የሆነው በአውሮፓውያኑ 1886 ግንቦት 4 በቺካጎ ሄይማርኬት በነበረው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ በፈነዳ ቦንብ የሞቱና የታሰሩ ሰዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው።
በአውሮፓውያኑ 2023 በተሰራ ጥናት በአለምአቀፍ ደረጃ 3 ነጥብ 62 ቢሊየን ላብ አደሮች ይገኛሉ።
ዘንድሮም በተለያዩ ሀገራት በድምቀት ይከበራል።
————እንኳን ለአለምአቀፍ የላብ አደሮች ቀን አደረሳችሁ!————












