። ። ። ። ። ። ። ። ።
እስራኤል የሊባኖሷ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች፡፡
የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ‘’እስራኤል ሽብር እየዘራች ነው’’ በሚል ማውገዟም ተሰምቷል፡፡
በደቡባዊ ቤይሩት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የእስራኤልን ትክክለኛ ባህሪ በግልጽ የሚያሳይ ነው ያለችው ኢራን፣ እንዲህ ዓይነቱ የወንጀል ድርጊት የሊባኖስ ህዝብን ከቆመበት ዓላማ አይበግረውም የሚል መግለጫ ሰታለች።
የሔዝቦላህ የፓርላማ ዓባል ኢብራሂም ሞውሳዊ የመንግስታቱ ድርጅት እስራኤልን እንዲያወግዝም ጠይቀዋል፡፡ የእስራኤል አየር ጥቃት የሊባኖስን ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ ነው ብለዋል የፓርላማ ዓባሉ፡፡
የሊባኖስ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን እንዲያቀርብ እና የጸጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግም አስገንዝበዋል።
ሄዝቦላህም ትጥቅ እንደማይፈታ ያሳወቁ ሲሆን፣ የቀጠናው ውጥረት መልኩን ሊለውጥ እንደሚችል ግን ዓለም ልትረዳው ይገባል በሚል አስጠንቅቀዋል የሄዝቦላህ ተወካይ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው ፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












