::::::::::::::::::::::::::::::::::
ሌስተር ሲቲ ባሳለፍነው ሳምንት በሊቨርፑል ከተሽነፈ በኋላ ሳውዝሃምፕተንን ተከትሎ ከሊጉ መውረዱን አረጋግጧል።
የአውሮፓውያኑ 2015-16 የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ ሌስተር፣ በሶስት ተከታታይ አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ከከፍተኛው የሊግ እርከን ተሰናብቷል።
ሩድ ቫንኒስትሮይ የሌስተር አሰልጣኝ የሆነው በህዳር ወር ሲቲቭ ኩፐርን በመተካት የ3 አመት ኮንትራት በመፈራረም ነበር።
ቀበሮዎቹ በሆላንዳዊው ስር ባደረጓቸው 20 ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻሉት 8 ነጥብ ብቻ ነው።ቫንኒስትሮይ ነገ ከሜዳቸው ውጪ ወልቭስን ከሚገጥሙበት ጨዋታ አስቀሞ በሰጠው
ቃለምልልስ “በክለቡ ስለመቆየቴ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ከቦርድ አባላት ጋር በቀጣይ ምን ማድረግ ይገባናል ብዬ ብጠይቃቸውም አትጋቢ ምላሽ አላገኘሁም ብሏል”።
አሰልጣኙ ከለቡን በሻምፒዮንሺፕ ወርዶም የማሰልጠን ተነሳስነት እንዳለውና፣ ወደ ፕሪምየር ሊግ የመመለስ ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል።
የቀበሮዎቹ ደጋፊዎች እስካሁንም ድረስ የመረረ ተቃውሞ የሚያሰሙት በአሰልጣኙ ሳይሆን በቦርድ አባሎቹ ላይ ነው።
ለክለቡ ውድቀት ተጠያቂ የሚያደርጉት እነሱኑ በመሆኑ ነገ በሞሊኒው ወልቭስን በሚገጥሙበት መርሃ ግብር “የቦርድ አባላት ክለባችንን ይልቀቁልን” የሚል ባነር የያዘ ሄሊኮፕተር በስታዲየሙ አናት የማብረር እቅድ እንዳላቸው ታውቋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












