April 18, 2025
የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በጸሎት፣ በስግደት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው። በቤተ-ክርስቲያኗ የስቅለት በዓል ሥርዓት በድምቀት ከሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል በልደታ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተ-ክርስትያን የተገኙት የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን በሃይማኖታዊ ሥርዓቱ መሰረት እያከበሩ ይገኛሉ።

በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ዕለተ አርብ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ ያለፈባቸው የስቃይና የመከራ ጊዜያት ስለፍፁም ፍቅር ሲል እንደሆነ ይታመናል።

በልደታ ማርያም ካቶሊክ ካቲድራል ቤተክርስትያን በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የስቅለት በዓል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል፣ ሊቀጳጳሳት፣ አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል። EBC
፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
ማስፈንጠሪ (ሊንክ) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ ![]()












