፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተወዳዳሪው ክለብ በኢኳዶሯዊው ተጫዋች ላይ ጠንካራ ፍላጎት ማሳየቱን ተዓማኒነት ያላቸው ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛል።
የ23 አመቱን ካይሴዶ ለማስፈረም አል ናስር ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑም ተነግሯል።
ሰማያዊዎቹ ተጫዋቹን ከሊቨርፑል ተጫርተው ከብራይተን ሲያስፈርሙት ተመሳሳይ የዝውውር ገንዘብ በማውጣት፣ በአማካኝ መስመርም የረጅም ጊዜ መፍትሔ እንዲሆን በማሰብ ነው።
ካይሴዶ በቼልሲ የረጅም ጊዜ ኮንትራት በመፈረሙም፣ ለየክርስቲያኖ ሮናልዶው አል ናስር ዝውውሩ ቀላል እንደማይሆንለት ይጠበቃል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












