፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ስፔናዊው የበርንማውዝ ተካላካይ ከክረምቱ የዝውውር መስኮት መከፈት አስቀድሞ በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች የሚታደን ሆኗል።
ሪያል ማድሪድ ከየትኛውም ክለብ በተሻለ ወጣቱን ተከላካይ የግሉ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ሲሆን፣ ተጫዋቹ ግን በፕሪምየር ሊግ የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
ሁሴን በዘንድሮው አመት ሳይጠበቅ ለአውሮፓ ስፍራ እየተፎካከረ በሚገኘው በርንማውዝ ድንቅ አቋል ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች ቀዳሚው ነው።
በርንማውዞች ተጫዋቹን በአምናው የክረምት ገበያ ከዩቬንቱስ ያመጡት ሲሆን ከአንድ አመት ግልጋሎት በኋላ አራት እጥፍ አትርፈው ልሸጡት ተዘጋጅተዋል።
የ20 አመቱ ዴያን ሁሴን በፕሪምየር ሊግ ለመቆየት መወሰኑ ተጫዋቹን በጥብቅ ለሚፈልጉት ቼልሲ እና ሊቨርፑል መልካም ዜና ሆኖላቸዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












