።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በብዙ የእግርኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ 2 ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው የሚደረጉ ይሆናል።
በሳንቲያጎ ቤርናቢዮ ሪያል ማድሪድ አርሰናልን የሚያስተናግድበት መርሃ ግብር ከፍተኛ ግምት የተሰጠው፣የሚዲያ ትኩረትን የሳበ ጨዋታ ነው።
በመጀመሪያው ዙር አርሰናል 3-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ ያለውን እድል ማስፋት ቢችልም፣ሎስ ብላንኮዎቹ ከነገሱበት መድረክ በቀላሉ አይወጡም የሚል ግምት ተወስዷል።
ካሳለፍነው ሳምንት አንስቶ የስነ ልቦና ጦርነት የከፈቱት የስፔን ሚዲያዎች፣በተለይም ማርካ አርሰናልን በማሳነስ ማድሪድ ውጤቱን ይቀለብሰዋል የሚለውን ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ ይገኛል።
የክለቡ የቀድሞ እና የአሁን ኮከብ ተጫዋቾችም በምሽቱ ጨዋታ ታሪክ ሊሰራ እንደሚችል በተደጋጋሚ ተናግረዋል።
የጨዋታው አጠቃላይ ውጤት በአሰልጣኝነት ስራቸው ላይ አደጋ ይጋብዛል የተባለባቸው አንቼሎቲ፣ ምንም እንኳን መረጃውን ቢያስተባብሉም ማድሪድ ተተኪያቸውን አሎንሶን መመልከት ጀምሯል።
የ15 ጊዜ የቻምዮንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ምንም እንኳን በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ውጤት ቀልብሶ ያለፈባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም፣ የ 3-0 ውጤትን ሲሻገሩ አልታየም።
በክለቡ የረጅም ጊዜ ታሪክ ይህን መሰል ውጤት የቀለበሰው ከግማሽ ምዕት አመት በፊት በፈረንጆቹ 1975 ነው። ያን ጊዜ በዚሁ መድረክ በእንግሊዙ ደርቢ ካውንቲ የደረሳባቸውን የ4-1 ሽንፈት ቀልብሰው ማለፍ ችለዋል።
አሰልጣኝ አንቼሎቲ ካሳለፍነው ሳምንት ሽንፈት ወዲህ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይገኛሉ አሁንም በሶስት የውድድር መስኮች የዋንጫ እድል ቢኖራቸውም ክለቡና ደጋፊዎቹ “የኛ ነው” ከሚሉት ቻምፒዮንስ ሊግ ምሽት ላይ የሚወጡ ከሆነ ጫናው ይበረታባቸዋል።
በሎስ ብላንኮዎቹ በኩል ዳኒ ሴባዮስ ከጉዳቱ አገግሞ የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ተዘጋጅቷል ኦሬሊዮ ቿሚኒ በተከታታይ በተመለከታቸው ቢጫ ካርዶች ሳቢያ ከጫዋታው ውጪ ሆኗል።
አንቼሎቲ እሁድ ዕለት በላሊጋው ዲፖርቲቮ አላቬስን በገጠሙበት ጨዋታ የተወሰኑ ተጫዋቾን ለማሳረፍ ችለዋል። ከፊት መስመር የጨዋታ መልክ የመቀየር አቅም ያላቸውን ቪኒ ጁኒየር፣ኪሊያን ምባፔ እና ሮድሪጎን ይጠቀማሉ።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












