6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በ25ኛ መደበኛ ስብሰባው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ማስፈጸሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የውሃ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡












