፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሃላፊነቱን ከለቀቀ በኋላ በተለያዩ ክለቦች እና ብሄራዊ ቡድኖች የአሰልጥነን ጥያቄ ቢቀርብለትም ቢያንስ ለአመት እረፍት እንደሚፈልግ አሳውቆ ነበር።
ማንችስተር ዩናይትድ ሩበን አሪምን ከመቅጠሩ አስቀድሞ ሳውዝጌትን በአማራጭነት ሲያጥጤን መቆየቱ አይዘነጋም።
ሳውዝጌት ከሶስቱ አናብስት ጋር ከተለያየ በኋላ 6.8 ሚሊየን ዩሮ ወጪ አድርጎ ባለድርሻ በሆነበት MAS INVESTMENT HOLDING ድርጅት ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን በንግድ ላይ በማድረግ በድርጅቱ ዳይሬክተር ሆኗል።
በተጫዋችነት በ ሚድልስ ቦሮ ክለብ የሚታወሰው ተከላካይ፣ አገሩን በአሰልጣኝነት እየመራ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ መቅረብ ቢችልም አሽናፊ መሆን አልቻለም።
ከአሰልጣኝነት ስራ ሙሉ በሙሉ ቢወጣም፣በዩ ኤፋ የቴክኒካል ጉዳዮች አማካሪነት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












