፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሦስተኛው የአፍሪካ ብየዳ ጉባኤ እና አለም አቀፍ ኮንፈረንስ “አፍሪካን ማብቃት፣ የብየዳ አቅምን ማጎልበት፣ ለቀጣናዊ ትብብር እና ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ቃል በዓድዋ ሙዚየም እየተካሄደ ነው ።
በጉባኤው የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሀመድ አብደላለም ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስተር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፣ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፉዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የብየዳ ዘርፍ አህጉሪቱ የምትፈልገወን እድገት ለማሳካት እና የአፍሪካ ሀገራትን በመሰረተ ልማት ስራዎች ለማስተሳሰር የሚያደርገው አስተዋጾኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
ጉባኤ በአፍሪካ የሚገኙ በብየዳ ዘርፍ የተሰማሩ ሙያተኞች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እና የተሻለ ስራዎች እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ተብሏል ።
ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የብየዳ ሙያ ውድድር ያካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በ- የአብስራ ብርሃኑ












