ኢትዮ ቴሌኮም በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚጠበቅበትን ቁልፍ ሚና አጠናክሮ በመጫወት ዜጎች ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽኖች እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በሁለቱ ሪጅኖች ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የኔትወርክ ማስፋፊያ ሥራ በማጠናቀቅ 114 ከተሞችን የዘመናዊው 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ኩባንያው በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ177 ጣቢያዎች ላይ የአቅም ማሳደግ (Upgrade) ስራ በማከናወን እንዲሁም 58 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 56 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት እንዲያጣጥሙ ለማድረግ ችሏል፡፡


በተመሳሳይ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ227 ጣቢያዎች ላይ አቅም በማሳደግ በማከናወን እንዲሁም 53 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 58 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ መቻሉን ገልጿል ፡፡












