:::::::::::::::::::::::::::
በዶሚኒካን ሪፐብሊክ የምሽት መዝናኛ ውስጥ ጣራ ተደርምሶ 184 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡
በሳንቶ ዶሚንጎ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የህይወት አድን ሰራተኞች በስፍራው በመሰማራት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመታደግ እየተረባበረቡ እንደሆነም ታውቋል፡፡
የዶሚኒካን ባለስልጣናት ጀት ሴት ተብሎ በሚጠራው የምሽት መዝናኛ ክለብ በደረሰው አደጋ ከባድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያዎች እንደዘገቡት እስካሁን ድረስ የማቾች ቁጥር ከተገለጸው በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን እየተናገሩ ይገኛል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ለተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን ማለታቸውን አልጀዚራ አስነብቧል ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












