:::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ፕሬዝዳት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጁባ የገቡት በሃገሪቱ የፖለቲካ አለመረረጋት ባለበት ወቅት ነው፡፡
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተከትሎ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውጥረትን አባብሶታል።
በዚህ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ወደምትገኘው ጎረቤት ሃገራቸው ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ያቀኑት ከዚሁ ተያያዥነት ላለው ጉዳይ ነው ተብሏል።
በደቡብ ሱዳን የርስበርስ ጦርነት እንዳይቀሰቅስ ስጋት ቢኖርም፣ የማቻር ደጋፊዎች በፈረንጆቹ 2018 የተፈረመው ስምምነት ማክበር ሰላምና መረጋጋትን ያመጣል የሚል እምነት አላቸው።
ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሙሴቬ ጋር ውይይት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮችም የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ለመመርመር ጁባ ደርሰዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












