የቦሊውዱ ተዋናይ እና ዳይሬክተር ማኖጅ ኩማር በ87 ዓመቱ አረፈ
ተዋናዩ በህንዷ የንግድ ዋና ከተማ ሙንባይ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ማለፉን የኮኪላበን ድሂሩባይ አምባኒ ሆስፒታል ዶክተሮች አሳውቀዋል ፡፡
ልጁ ኩናል ጎስዋሚም ለረዥም ዓመታት የጤና እክል አባቱን እንደገጠመው ተናግሯል ፡፡ በህንድ ምድር የአርበኛ ወይንም የአገር ወዳድ ፊልሞችን በምስራት ከፍተኛ እውቅና በ1960ዎቹና 1970ዎቹ እንዳገኘም ይነገርለታል፡፡
የኩማርን ህልፈት ተከትሎ አድናቂዎቹ፣ዝነኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ሀዘናቸውን በመግለጽ ለይ ይገኛሉ፡፡የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም “የህንድ ሲኒማ ምልክት”ብለውታል ኩማርን፡፡

አብዛኞቹ የህንድ ተዋናያን ማኖጅ ኩማር በዘርፉ ላይ ለመቆየት አቅም እንደፈጠረላቸውም አስታውሰዋል፡፡ አክሻይ’ ኩማር የኩማርን ፊልሞች እያየ ማደጉን ካስታወሱ ዝነኞች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ በህንድ ሲኒማ ውስጥ ወርቃማውን ጊዜ የፈጠረ ነው በሚልም ሲገልጹት ተስተውሏል ፡፡
በፈረንጆቹ 1937 በሰሜናዊ ፑንጃብ ግዛት የተወለደው ኩማር ለህንድ ፊልም ማደግ ከፍተኛ ሚና የነበረው ነው ተብሎለታል ፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው ፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












