በዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች 3ተኛ ዓመታቸው ላይ በሙያቸው ማህበረሰቡን የሚያገለግሉበት አሰራር ሊዘረጋ መሆኑ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡
የመምህራን እጥረት፣ጥራትና ብቃት በትምህርት ስርዓቱ የፈጠረውን ጫና ለማቃለል በዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች 3ተኛ ዓመታቸውን ላይ ማህበረሰቡን በሙያቸው የሚያገለግሉበት አሰራር ከ2019 ጀምሮ ተግራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ አንስተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ ይህንን ንግግር ያደረጉት ትምህርት ሚኒስቴር የ12 ክፍል ውጤት ማሽቆልቆል ምክንያትን ትኩረት ያደረገውን ጥናት ለኢፌድሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰው ሀብት ልማት፣ስራ ስምሪት እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ላይ የተስተዋለው የውጤት ማሽቆልቆል እንደ ህዝብ ያጋጠመውን የሞራል ኪሳ አጉልቶ ያሳየ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ የገጠመውን ችግር ለመቅረፍ ከተያዙት እቅዶች መካከል መምህራን አቅምና ኑሮ ላይ መስራት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
የመምህራን ኑሮ ከማሻሻል ረገድም የመምህራን ባንክ በማቋቋም ከባንክ ብድር እንዲያገኙ በማድረግ ኑሮአቸውን የሚያሻሽሉበት አሰራር ሊዘረጋ ነው ተብሏል፡፡
ኩረጃ፤ ፍትሀዊ የትምህርት መሰረተ ልማት አቅርቦት አለመኖር፣ የመምህራን እጥረት ና የብቃት ማነስ፣ኮቪድ19ና በየአከባቢ የሚፈጠሩ ግጭቶች ለውጤቱ መቀነሱ ማነቆ መሆናቸው ትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው ጥናቱ ተመላክቷል፡፡
በ-ሰላም ይልማ












