፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 22ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ጥያቄ ተነስቶበት ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶበታል።
በተለይም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በመከተል ወደ መደበኛ አስተዳደር እንዲገባ የሚያደርገው አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በአብላጫ ድምጽ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል።
አዋጁ የጊዜያዊ አስተዳደሩን የቆይታ ጊዜ በማራዘም በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርግ እንደሆነም ተነግሮለታል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ












