:::::::::::::::::::::::::::::::
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል አዛዥ ጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “ሂሚዲቲ” ሰራዊታቸው ከዋና ከተማዋ ማፈግፈጉን ተከትሎ ነው ይህንን ያሉት።
ባለፈው ሳምንት በካርቱም ከተማ መዳረሻ እና በከተማዋ በተደረገ ጠንካራ ውጊያ የመከላከያ ሃይሉ የፈጥኖ ደራሹን ይዞታ ማስለቀቁ በሰፊው ተዘግቧል።
የድል ባለወረፋ የሆኑት የመከላከያው አዛዥ ሌተና ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ሙሉ ለሙሉ ከዋናው ከተማ ማስለቀቃቸውን ተናግረዋል።
ጦራቸው ድል ከሆነ በኋላ በማህበራዊ የትስስር ገጽ ብቅ ያሉት ጄኔራል ዳጋሎ ከዋና ከተማው በወታደራዊ ስትራቴጂ ማፈግፈጋቸውን ተናግረዋል አያይዘውም ጦርነቱ አላበቃም ብለዋል።
ሁለተኛ አመቱን የተሻገረው የሱዳን የርስበርስ ጦርነት 50 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሃብ አገልጧል። 12 ሚሊየን የሚሆኑትን ለስደት ሲዳርግ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን ህይወት ቀጥፏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












