፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ በሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ ምድረገነት ቀበሌ የተገነባው ‘ኢፋ ቦሩ’ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና ሌሎች የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና የሸበዲኖ ወረዳ ነዋሪዎች መገኘታቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውቋል።

ትምህርት ቤቱ 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።












