።።።።።።።።።።።።።።።።
በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያ ዲፕሎማቶችን በማሠማራት ባደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተጠቅሷል።
በተያያዘ መንግሥት ጃፓን በሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወደ አልተፈጸመባቸው ሀገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ጥሪ መቅረቡን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።












