፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 13 2017| NBC ETHIOPIA- በእንግሊዝ መቀመጫውን ያደረገው የሳተላይት ምስሎች አጥኚ ቡድን እንዳስታወቀው ሩሲያ ለሰሜን ኮሪያ ለተከታታይ ወራት ግዙፍ መጠን ያለው ነዳጅ እየሰጠች መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢሮ ኃላፊ ዴቪድ ላሚ በበኩላቸው ፒዮንግያንግ ወታደሮቿን ወደ ሞስኮ በመላኳ ምላሹ “ነዳጅን የማግኘት ክፍያ መሆኑ ነው” ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ሰሜን ኮርያ በኒውክሌር መሳርያ ምርት እና አጠቃቀሟ የተነሳ ከየትኞቹም ሀገራት በነጻ ገበያ ሒደት ነዳጅ እንዳይሸጥላት በተመድ ማዕቀብ እንደተጣለባት አይዘነጋም፡፡
ይሁንና ከባለፉት ስምንት ወራት ወዲህ በ43 እጥፍ የነዳጅ ታንከሮችን ከሩሲያ ማግኘት እንደቻለች የቢቢሲ ዘገባ ያስረዳል፡፡
የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከመቼውም ጊዜ በላይ ግንኙነታቸው መጠናከሩም ተጠቅሷል፡፡
ከሁለት ቀናት በፊት ፑቲን ለሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የእንስሳት ፓርክ ደቦል አናብስትን እና ከሰባ በላይ እንስሳትን በስጦታ መልኩ ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












