፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 11 2017| NBC ETHIOPIA- የዘንድሮው አለም አቀፍ የህፃናት ቀን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ 35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከረ ነው።
ሁነቱ ”ህፃናት የሚሉት አላቸው እናድምጣቸው” በሚል መሪ ቃል ነው በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በመርሀግብሩ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ አለማቀፍ የህጻናት መብት ድንጋጌን ፈርማ ከተቀበለች ወዲህ የህጻናትን መብት ለማስከበር አበክራ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸው፥ ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን ለመጠበቅ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።
ህጻናት ድምጻቸው እንዲደመጥ፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ በስነ-ምግባር የታነጹ እና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ ለማድረግ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በንቃት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የህጻናትን መብቶችን ለማስከበር በሚከናወኑ ስራዎች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እና ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ሚኒስትር ኤርጎጌ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲንን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች ፣ የህፃናት ፓርላማ ተወካዮች፣ታዳጊ ህጻናት፣ ወላጆችን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












