፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 06 2017| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ቅባት እህሎችና ቅመማቅመም ላኪዎች ማህበር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 13ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ ሊያካሂድ ነው ተባለ።
ጉባኤ ከ22 እስከ 25 ሀገራት እና ከ430 በላይ የሀገር ውስጥ ላኪዎች እንደሚሳተፉበት ተጠቁሟል።

በባለፈው በጀት ዓመት ከጥራጥሬና የቅባት እህሎች ከፍተኛ የወጪ ንግድ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል መላኩ ተገልጿል።
የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም በዘርፉ ላይ የሚታዩ የጥራትና የዋጋ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በ-ሰላም ይልማ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












