፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 03 2017| NBC ETHIOPIA- የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከኪነ-ጥበብ እና ስነ-ጥበብ ዘርፍ ማህበራት እና ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ይገኛል።
ኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ለሁለተናዊ ልማት እና ለሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ሀሳብ ምክክሩ እየተካሄደ ሲሆን በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሀገራችን ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በምክክሩ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዓለማችን ሀያል የሚባለት ሀገራት ፊልሞቻቸውንና ሙዚቃዎቻቸውን በመጠቀም ዜጎቻቸውን በሚፈልጉት ሀገራዊ ህልም ከመቅረፃቸውም ባሻገር በዓለም ህዝቦች ዘንድ አስፈሪ ሁለንተናዊ ጀግኖችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ሆነው ለመታየት ችለዋል ብለዋል።

ይህም በከነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ የላቁ ከመሆናቸውም ላይ በኢንቨስትመንት እና በቱሪስት ተመራጭ መዳረሻዎች ሊያደርጋቸውም ችሏል ሲሉ ተናግረዋል።
መንግስት በአሁኑ ወቅት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የባህልና የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ምቹና ሊያሰራ በሚችል ሁኔታ መደራጀቱ ከመድረኩ ሲመላከት ስራውን ለማሳለጥ የሚያግዙ በርካታ መሰረተ ልማቶች በተናጠልና ከትልልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች ጋር ተካተው ተብሏል።

ምንም እንኳ እስከአሁን በዘርፉ የተሰሩት ስራዎች አበረታች ቢሆኑም፤ ባህልን፣ ኪነ-ጥበብን፣ሥነ- ጥበብን እንደ ትልቅ መሳሪያ በመጠቀም ለአገር ገጽታ ግንባታ፣ ለትውልድ ቀረጻ፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ዘላቂ ሰላምን ደረጃ በደረጃ ለማስፈን፤ የህዝቦች የእርስ በእርስ ትስስርና አንድነት በመጠቀም ዘላቂ ውጤቶችን ከማስመዝገብ አንጻር አሁንም በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩ ተገልጿል።
ዘርፉን ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ለማዋል ያስችል ዘንድ ክፍተቶችን በመገንዘብ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
ሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ ንቅናቄ በመላው ሀገሪቷ ከህዳር 7 እስከ የካቲት 7 ድረስ በተለያዩ መሰናዶዎች ይካሄዳል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












