፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 23 2017| NBC ETHIOPIA-በኢትዮጵያ በ2016/17 በጀት አመት የወባ ወረርሺኝ እየተስፋፋ መምጣቱ ተገልጿል።
በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 26ተኛው አመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የወባ ወርሽኝ፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጨምሮ የአይምሮ ጤና እክል እየተስፋፋ መምጣቱን ነው የተናገሩት።
ችግሩን ለመቅረፍ በተለያዩ የጤና መስኮች ርብርብ ቢደረግም ያልተሰሩ ሰፊ ስራዎች በመኖራቸው የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ፣ የቅድመ ካንሰር ምርመራ፣ ክትባትን ማስፋፋት ላይ ይበል የሚያሰኝ ስራ መሰራቱን እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በ2016 በጀት አመት ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን የወባ በሽታ ታማሚዎች ህክምናን ማግኘታቸውን አንስተዋል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












