፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 30 2017| NBC ETHIOPIA- “የትምህርት ቤቶች ምገባ ለጤናማ እና ዘላቂነት ላለው የአፍሪካ ከተሞች” በሚል መሪ ቃል የ6ኛው Milan Urban Food Policy forum መክፈቻ ተካሂዷል።
በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ በልጆቻችን እና በከተማችን ወደፊት ላይ እየሰራን ነው በዚህም በከተማችን በርካታ ስኬትን ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።

በትምህርት ቤቶች ምገባ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በአዲስ አበባ ብቻ በ 255 ትምህርት ቤቶች ከ 800 ሺ ህፃናት በላይ መድስ የተቻለ ሲሆን ለ16ሺ እናቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ብቻ በቀን ሶስት ጊዜ ተማሪዎችን የሚመግቡ 21 ማዕከላት የተቋቋሙ ሲሆን በቀጣይ ይህንን ለማስፋት ይሰራል ተብሏል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












