፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 27 2017| NBC ETHIOPIA- የ6ኛው ዙር ቀሪና እና ድጋሚ ምርጫ ያሸንፉ አዲስ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል፡፡
አባላቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም.፤ በተካሄደው ምርጫ የተመረጡ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው ቃለ-መሀላ የፈጸሙት፡፡

በዕለቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ቴዎድሮስ ምህረት ቃለ-መሃላውን ያስፈጸሙ ሲሆን አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላትም ስራቸውን በሚጀምሩበት ወቅት በሕገ-መንግስቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እንዲሁም ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ ስራቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












