፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 23 2017| NBC ETHIOPIA- የአራኑ የመንፈሳዊ መሪ እስራኤል ሼክ ሀሰን ነስረላን ልትገድላቸው ማሴሯን አወቀው ነስረላን አስጠንቅቀው እንደነበረ ተነግሯል፡፡
ለሰይድ ሀሰን ነስረላና ለኢራኑ መፈንሳዊ መሪ አያቶላ ዓሊ ሰይድ ካሚኔይ ቅርበት ያላቸው ሶስት ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት እንደገለፁት የሄዝቦላው መሪ ከመገደላቸው ከቀናት በፊት የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ ነስረላን ሊባኖስን ለቀው ይወጡ ዘንድ ቀድመው ማስጠንቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከባለፈው ቅዳሜ ወዲህ በተለየና በስውር ስፍራ መቀመጣቸው የሚነገርላቸው የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አይቶላህ ዓሊ ሰይድ ካሚኔይ በእስራኤል ላይ ሁለት መቶ በላይ ሚሳይሎች እንዲተኮሱ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












