፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA-በሱዳን ሰባት ግዛቶች ውስጥ በኮሌራ በሽታና ጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ390 በላይ መድረሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡
እንደ ሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ በጎርፍ አደጋ 205 ሰዎች ሲሞቱ ፤ በኮሌራ ደግሞ 185 ህይወታቸው አልፏል፡፡ በከሰላ፤ ናይል ወንዝ እና ገዳሪፍ በሚባሉ ግዛቶች 268 አዲስ የኮሌራ ኬዝ መገኘቱም ታውቋል፡፡

በሱዳን የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 26,000 ቤቶች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ ፤ 33,000 ቤቶች በከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡
የዓለም አቀፉ ስደተኞች ደርጅት እንዳስታወቀው ከባለፈው ሰኔ ጀምሮ ከ 18 የሀገሪቱ ግዛቶች ውስጥ በ15ቱ የሚገኙ 172,000 ሱዳናውን ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡
በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እየተናጠች በምትገኘው ሱዳን የጎርፍ አደጋና ኮሌራ በሽታ መከሰቱ ሁኔታውን አስከፊ አድርጎታል ሲሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየገለጹ ነው፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
በ – ቶማይ መኮንን
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












