፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የውጤቱን ይፋ መደረግ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ- የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ከተፈታኞቹ ውስጥ 29 ሺህ 736 ያህሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን ወስደዋል ነው ያሉት፡፡ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ከሌሊቱ 6 ሠዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡












