፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የ2016 የበጀት አመት የእቅድ አፈጻጸምና የሰራተኞች የእውቅና መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በመገባደድ ላይ በሚገኘው 2016 523 አደጋዎች በአዲስ አበባ መከሰታቸውን አስታውቋል።
በነዚህም አደጋዎች ሊከሰት የነበረ የ156 ሰዎች ሞትን ማስቀረት ተችሏል የተባለ ሲሆን ከ37 ቢሊየን ብር በላይም ከውድመት ማዳኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በ2017 የበጀት አመትም የሚከቱ አደጋዎች ቀድሞ ለመከላከል የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
በ-አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












