፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA-አሜሪካ የሀማሱን መሪና ሌሎች አምስት የሀማስ መሪዎችን መክሰሷ ተሰምቷል፡፡
ሀማስን ይመሩ ዘንድ አዲስ የተመረጡ ያህያ ሲንዋር በጋዛ ሰርጥ የምድር መደበቂያ ውስጥ እንሚኖር ይነገራል፡፡
በሀማስ አምራርነት የቁንጮውን ስፍራ ከያዙት ሰባት ሰዎች ሀኒያ ዴይፍና ኢሳ መሞታቸው ሲገለጥ እስካሁን አራቱ ዋና መሪዎች አሉ ነው የሚባለው በቅርቡ የሀማስ ሀይሎች ስድሰት የእስራኤልን ታጋቾች ገድለው ማምለጣቸውን ተከትሎ ከተገደሉት ስድስቱ አንደኛው አሜሪካዊ እንደነበር ይታወቃል፡፡
አሜሪካ የዜጋዋ መገደል ሲያንገበግባት በያህያ ሲንዋርና በሌሎች አምስት የሀማስ ቀንደኛ መሪዎች ባለቻቸው አካላት ላይ ክስ መመስረቷን የታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












