፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA- ምድረ ቀደምት በሆነችው ኢትዮጵያ የተባበረች አንድ የሆነች አፍሪካን ለመፍጠር በማለም አጀንዳ 2063ንም ለማሳካት የተጀመረው ውጥንን ለማስቀጠል በሚል ነው ጉባኤው እየተካሄደ የሚገኘው።
አዲስ አበባ ከተማም ይህን ትልቅ እድል በማግኘት ፎረሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ማዘጋጀቷ ከቱሪዝም ገቢ አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተጠቁሟል።
ፎረሙ የአፍሪካ ከተሞች ለዜጎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ ማድረግን በሚመለከት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረግበታል።
ለሶስት ቀናት በሚቀጥለው በዚህ መድረክ በመክፈቻው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መሪዎች እና ልዑካን ታድመውበታል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












